በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የ2018 የክረምት STEM ስልጠና ተጠናቀቀ ።

News news
2026-09-02 07:06:26

ከስልጤና ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም  ከማረቆ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ኢንዱስትሪ  ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም / ፕሬዚዳንት  ተወካይና የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር ሙሀባ ኑረዲን  ተማሪዎች የነገው ሀገር ተረካቢዎች በመሆናቸው  በመደበኛ ትምህርታቸው ብቻ ሳይገደቡ በተግባራዊ ትምህርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በፈጠራ ሥራዎች የላቀ ብቃት እንዲያገኙ በማድረግ ወደላቀ ደረጃ ደርሰው  የሚታዩና ማህበረሰብን የሚጠቅሙ እንዲሆኑ ከወዲሁ  በSTEM  ስልጠና መሰጠቱ ክህሎታቸውን  ለማሳደግ ያለው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን  ገልጸዋል።
ተማሪዎች በፈጠራ ስራዎች ውጤታማ ለመሆን በትዕግስትና በጽናት መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የቴክኖሎጂ  ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይና የዩኒቨርሲቲው የኤሌክትሮኒክስ  ትምህርት አስተዳደር ዳይሬክተር  መምህር ጀማል ዙቤር በበኩላቸው ተማሪዎች በዚህ  መርሀ ግብር ስልጠና በSTEM (Science, Technology, Engineering and Mathematics) ዘርፎች ላይ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን  ትምህርት  በተግባር  እውቀት  ያገኙበት  እና  ክህሎታቸውን  የያዳብሩበት ስልጠና  እንደሆነ እምነታቸውን   ገልጸዋል።
ተማሪዎቹም በነበራቸው  ቆይታ ተገቢውን እውቀት እንዳገኙ  እና ያገኙትን ዕውቀት በልምምድ በማዳበር ሀገራቸውንና ህዝባቸው የሚጠብቁባቸውን ለመወጣት እንደሚጥሩ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም  ለሰልጣኝ ተማሪዎች የዕውቅና ሰርተፊኬት በመስጠት መርሀ ግብሩ ተጠናቋል ።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

22-779293.jpg 33-866079.jpg 44-947341.jpg 55-85595.jpg