በየደረጃው የሚሰጠው የትምህርት አሰጣጥ ላይ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጡ ረገድ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ።

News news
2026-10-17 10:33:44

ዛሬ የተጠናቀቀው ይሀው ስልጠና Leaders in Teaching Ethiopia (LiTE) ፕሮግራም ውስጥ EDT እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ መካካል በተደረገው የትብብር ስምምነት መሰረት ከስልጤ እና ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም ከማረቆ ልዩ ወረዳ ለተወጣጡ  ርዕሳነ-መምህራን፣ ለእጩ ሴት የትምህርት አመራሮች እንዲሁም ለትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች ሲሰጥ ነበር።

የስልጠናው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ጀማል ሬድዋን ሰልጣኞች በስራቸው የሚመሯቸውን የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ መርተው የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ሰልጣኞች ከስልጠናው ባገኙት ዕውቀት የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥና ብቁ ዜጋ ለማፍራት እንዲተጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ስልጠናው በዩኒቨርሲቲው ትምህርትና ስነ-ባህሪ ት/ቤት ዲን መ/ር ሱልጣን ሁልጫፎ ተሰጥቷል።

 

ዕውቀት ለልህቀት

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

2-97491.jpg 3-867348.jpg 4-26622.jpg 5-292420.jpg