የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ር ጀማል ሬድዋን ስልጠናው ቀጣይ ለታቀደው የተማሪ ውጤት ማሻሻል እና የርዕሳነ-መምህራንን አቅም ለመገንባት በትኩረት መሰራት አለባቸው በተባሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልፀዋል ።
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በየደረጃው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የLiTE ፕሮግራም የEducational Development Trust (EDT) አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ፋንታሁን የስልጠናው ዓላማ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች የትምህርት ጥራት፣ ተገቢነት እንዲሁም ኃላፊነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የትምህርት አመራሮች ተፅዕኖ ፈጣሪ አመራር እና የለውጥ መሪ ለመሆን በትኩረት በመስራት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።
የትምህርት ጥራትንና እና የተማሪን ውጤት ለማሻሻል የመጀመሪያውን ድርሻ የሚወስዱት መምህራን በመሆናቸው እራሳቸውን በቴክኖሎጂ በማብቃት የመማር ማስተማር ብቃታቸውን ማሳደግ ይችላሉ ብለዋል።
ስልጠናው Leaders in Teaching Ethiopia (LiTE) ፕሮግራም ውስጥ EDT እና ወራቤ ዩኒቨርሲቲ መካካል በተደረገው የትብብር ስምምነት መሰረት ከስልጤ እና ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም ከማረቆ ልዩ ወረዳ ለተወጣጡ ርዕሳነ-መምህራን፣ ለእጩ ሴት የትምህርት አመራሮች እንዲሁም ለትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች በመሰጠት ላይ ነው።
ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ