የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የወራቤ አማና/ቃል ኪዳን ቤተሰብ ትስስር ፕሮጀክት የትውውቅና የምስረታ በዓል ተካሄደ።
ጥር 21፣ 2018 (ወራዩ/ ህ /አ /አ /ግ) የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የወራቤ አማና/ቃል ኪዳን ቤተሰብ ትስስር ፕሮጀክት የትውውቅና የምስረታ በዓል ተካሂዷል።
በመርሃግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ተማሪዎች በፍቅርና በቤተሰባዊነት እንዲታቀፉ ማድረግ የፕሮጀክቱ አላማ መሆኑን ተናግረዋል።
ማህበራዊ ትስስራችን ሲጠናክር ሀገር ትጠነክራለች ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተገኘውን ተሞክሮ ከስልጤ ህዝብ እንግዳ ተቀባይነት ጋር በማስተሳሰር የተጀመረ መሆኑንም ገልጸዋል።
ትስስሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተረጋግተው እንዲከታተሉ ከማስቻሉም ባለፈ የተማሪ ቤተሰቦችም በልጆቻቸው ጉዳይ ሀሳብ እንዳይገባቸው የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰላምና ውጪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ክብርት ወ/ሮ ውበቴ ታደገ ፕሮጀክቱ ለሀገረ ግንባታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሀገሪቱ ከአራቱም ማዕዘናት ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተማሪዎች የባይተዋርና የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር የማህበራዊ ሀብት ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ ትዕዛዙ ደሳለኝ ፕሮጀክቱ ህብረ ብሄራዊ አንድነትና እሴት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ የሀገራችንን ሰላም በማጠናከር ሂደት ፋይዳው የጎላ የሰላም ድልድይ የሚሆን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመርኃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው እና የወራቤ ከተማ አመራሮች የከተማው ነዋሪዎች ተማሪዎችን እንደ ወላጅ ተቀብለው ለመንከባከብ የቃል ኪዳን ስምምነት ከተማሪዎች ጋር ተፈራርመዋል።
ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!
• Website: https://www.wru.edu.et/
• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru
• YouTube: https://www.youtube.com/@werabeuniversityofficialtu8944