ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የስልጤ ዞን አስተዳደር የግብርና የምርምር ስራዎችን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

News news
2026-01-28 07:04:02

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የስልጤ ዞን አስተዳደር የግብርና የምርምር ስራዎችን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ጥር 18፣ 2018 (ወራዩ/ ህ /አ /አ /ግ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና የስልጤ ዞን አስተዳደር የግብርና የምርምር ስራዎችን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል እና የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ተፈራርመዋል።  የስምምነቱ ዓላማ የተለያዩ የግብርና ምርቶች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በሀገር ውስጥና በውጭ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል። የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ዩኒቨርሲቲው ስምምነቱን በጋራ ወደ ተግባር በመቀየር ለውጤታማነቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱ የግብርና ስራዎች በምርምር ሲደገፉ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድጉ ገልጸዋል።

በመግባቢያ ስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት አካላትና የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ተገኝተዋል።

ዕውቀት ለልህቀት

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/@werabeuniversityofficialtu8944

 

photo_2026-01-27_19-59-44-577905.jpg photo_2026-01-27_19-59-49-146203.jpg photo_2026-01-27_19-59-52-182541.jpg photo_2026-01-27_19-59-54-577479.jpg photo_2026-01-27_19-59-57-898723.jpg photo_2026-01-27_20-00-00-426369.jpg photo_2026-01-27_20-00-03-822714.jpg