ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የፕሮግራም ዕውቅና (Program Accreditation) አጠቃላይ መስፈርቶች ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው

News news
2025-12-31 12:11:00

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የፕሮግራም ዕውቅና (Program Accreditation) አጠቃላይ መስፈርቶች ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው

ታህሣሥ 21፣ 2018 (ወራዩ/ ህ /አ /አ /ግ) ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (ETA) ጋር በመተባበር ለአካዳሚክ አመራሮችና መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው ትምህርቶች ዓለም አቀፋዊ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ በማድረግ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጎችን ለማፍራት የሚደረጉ ጥረቶችን የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለፕሮግራሞቹ ሙሉ እውቅና ለማግኘት የውስጥ ዝግጅቱን አጠናክሮ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ለዚህም በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

በፕሮግራሞቹ ቀጣይነት ያለው የውስጥ ጥራት ቁጥጥር (Internal Quality Assurance) ስርዓት ተዘርጋቶ የመማር-ማስተማር ሂደቱን ወደ ውጤት ተኮር እና ጥራትን ማዕከል ያደረገ ስርዓት ማሸጋገር ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ስልጠናው በፌደራል ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት Program Accreditation ዴስክ ኃላፊ ወይዘሮ ስርጉት ሽመልስ እና በዘርፉ ባለሙያ አቶ አዳነ አረጋይ እየተሰጠ ሲሆን በነገው ዕለትም ቀጥሎ ይውላል።

 

ዕውቀት ለልህቀት

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/@werabeuniversityofficialtu8944

 

photo_2025-12-30_13-07-30-524936.jpg photo_2025-12-30_13-07-33-528744.jpg photo_2025-12-30_13-07-35-658910.jpg photo_2025-12-30_13-07-37-927327.jpg photo_2025-12-30_13-07-38-48357.jpg photo_2025-12-30_13-07-39-461775.jpg photo_2025-12-30_13-07-40-658413.jpg photo_2025-12-30_13-07-59-41693.jpg photo_2025-12-30_13-08-03-374751.jpg