2ኛዉ ዙር የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱን ቀጥሏል

News news
2025-12-10 08:52:18

2ኛዉ ዙር የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱን ቀጥሏል

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በእዉቀት ፣ በክህሎትና በአመለካከት የበቁ ዜጎችን ማፍራት ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

በሀገር ደረጃ ሪፎርም ከተደረጉ ተቋማት መካከል የትምህርት ሴክተሩ አንዱ ስለመሆኑ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ዉስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም ስለመደረጉም አስታዉሰዋል፡፡

በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮና በትኩረት መስክ ተለይተዉ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በመፈጸም ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡

የኮምፕሬሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች በግብርና ፣ በኢንዱስትሪው ፣ በአገልግሎትና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢንዱስትሪው የሚፈለገውን ብቁ የሰለጠነ ሰዉ ኃይል የማፍራት ተልዕኮ እንደተሰጣቸዉም ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በትብብር የመስራት ፣ የልምድ ማጋራትና ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ማከናወንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን ለማስፋት የጠቅላላ ጉባኤዉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ የተሰጣቸው ሀገራዊ ተልዕኮ ትብብርን በማጠናከር በብቃት ለመወጣት የጠቅላላ ጉባኤዉ ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም ነው ፕሬዜዳንቱ የገለጹት፡፡

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል የኮምፕርሄሲቭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስለወራቤ ከተማ አጠቃላይ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በጠቅላላ ጉባኤዉ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ከ 20 በላይ የኮምፕሬሄንሲቭ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡

 

1-532455.jpg 2-289669.jpg 3-753470.jpg 4-92694.jpg 5-388219.jpg 6-446828.jpg 7-413490.jpg 8-150643.jpg 9-22802.jpg