ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በቁልፍ የውጤት አመልካቾች (KPIs) ላይ የግብ ስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሄደ ።
ጥቅምት 11፣2018 (ወራዩ /ህ /አ/ አ/ ግ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በቁልፍ የውጤት አመልካቾች (KPIs) ላይ የግብ ስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂዷል።
ስምምነቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ከአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አግልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ረ/ፕሮፌሰር አንዋር አህመድ ፣ ከአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት መ/ርት አለዊያ ሀሰን እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ መ/ር ከድር ሽፋ ጋር ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን ምክትል ፕሬዚዳንቶቹና የጽ/ቤት ኃላፊው በየዘርፋቸው ከሚገኙ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ኮሌጂ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ተፈራርመዋል።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ባለፈው ዓመት የቁልፍ ውጤት አመልካቾች ላይ ይበል የሚያሰኝ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመትም የግብ ስምምነት መፈራረማችን እንደተቋም የተቀበልነውን ኃላፊነት በትኩረት አከናውነን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ስለሚረዳን ሁሉም በየዘርፉ የሚጠበቅበትን መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በመጨረሻም ስምምነቱን ሁሉም ባለሙያዎች በየደረጃው ከሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚፈራረሙ እና አፈጻጸሙ ላይ አስፈላጊው የድጋፍና ክትትል ስራ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚሰራም ተገልጿል።
ዕውቀት
ለልህቀት
ወራቤ
ዩኒቨርሲቲ