ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት አሰጣጥ እና ደንብ አተገባበርን አስመልክቶ ለባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

News news
2025-10-07 11:42:12

መስከረም 12፣ 2018 (ወራዩ/ ህ/ አ/አ/ግ)  ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት አሰጣጥ እና ደንብ አተገባበርን አስመልክቶ ለባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመሯል።

የዩኒቨርሲቲው የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ርት ከይሮ አሰፋ  የስልጠናዉ ዓላማ  ባለሙያዎች የቤተ መጽሐፍቱን ሙያዊ  አሰራር እና አተገባበር  መመሪያ ጭብጥ በመረዳት ከአገልግሎት  አሰጣጥ  ጋር ያሉ ክፍተቶችን በማረም  በዕውቀት እና በክህሎት የተደገፈ ፍትሃዊ እና ተደራሽ  አገልግሎት  እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታ  ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።

መ/ርት ከይሮ አክለዉም  የዩኒቨርሲቲያችን  ቤተ -መጻሕፍት   ዘመኑን የዋጀና ለአንባቢያን  ቀልጣፋ እንዲሁም  የተገልጋይ እርካታን ለማሟላት  የሚያስፈልገውን አገልግሎት ለመስጠት ስልጠናው አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል ።

ስልጠናው ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት በመጡት በወ/ሮ ብዙወርቅ ተስፋዬ እና በአቶ ስለሺ  ወርቁ እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ለተከታተይ አራት ቀናት ይቆያል።

ዕውቀት ለልህቀት

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram: https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/@werabeuniversityofficialtu8944

552812260_1239054341573796_1533449438503409499_n-411081.jpg 550581694_1239054308240466_8793859527852929088_n-22400.jpg 553395948_1239054258240471_7436330710959394159_n-958216.jpg 550329881_1239054194907144_4720569805584294005_n-157557.jpg 552461148_1239054118240485_8355185439680783354_n-894176.jpg 553303214_1239054061573824_4865668196257207716_n-229353.jpg