መስከረም 10፣ 2018 (ወራዩ/ ህ/ አ/አ/ግ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በAuditable
Pharmaceutical Transactions & Services (APTS) ዙሪያ ለሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲ ባለሙያዎች እና
ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር ጀማል ሬድዋን
የስልጠናው ዓላማ በክህሎትና በዕውቀት የበቁ የጤና ባለሙያዎችን በማፍራት በዘርፉ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው በማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ስራ አተገባበር፣ ሪፖርት አደራረግ፣ ሽያጭ አመዘጋገብና
በAPTS አተገባበርና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ትኩረት ማድረጉን ተናግረዋል።
ስልጠናዉ ለፋርማሲ ባለሙያዎች፣ ለሂሳብ ሰራተኞች፣ ለንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች፣
ለግዥ እና ለሰው ሀብት ባለሙያዎች እንዲሁም ከዘርፉ ግንኙነት ካላቸዉ የተለያዩ ስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው
ነገም ቀጥሎ ይውላል።
ዕውቀት
ለልህቀት
ወራቤ
ዩኒቨርሲቲ
መረጃዎቻችንን
በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!
•
Website: https://www.wru.edu.et/
•
Telegram: https://t.me/werabeuniversitywru
•
YouTube: https://www.youtube.com/@werabeuniversityofficialtu8944