በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የኢኮኖሚ
ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ሰራተኞች ስልጠና መሰጠት ጀመረ።
ለ25 ቀናት የሚሰጠዉ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የኢኮኖሚ
ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ሰራተኞች ስልጠና ዛሬ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ልዩ
ረዳት አቶ መሀመድ አማን በስልጠናው መክፈቻ መድረክ ላይ ተገኝተዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን መረጃ የሀገር ሀብት ስትራቴጂክ ግብዓት በመሆኑ ትክክለኛዉን መረጃ በመሰብሰብ እና በመተንተን ተዓማኒነት ያለዉ መረጃ ተደራሽ ማድረግ ለሀገር ትልቅ አበርክቶ አለው ብለዋል።
አቶ መሀመድ አማን አክለዉም ስልጠናዉ እስኪጠናቀቅ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሆሳዕና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን አሰፋ ሰልጣኞች ከስልጠናው ጊዜ ጀምሮ በእያንዳንዱ የመስክ ስራ ክንዉን ወቅት የመረጃ መሰብሰብ እና ማስተባበር ተግባራቸው ሙያዊ ብቃታቸዉን በማሳደግ እና ኃላፊነትን በግል እንዲሁም በጋራ በመወጣት ቁርጠኝነታቸዉን በማሳየት ቆጠራዉን ከዳር ለማድረስ የበኩላቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል ።
በመስክ ስራ ክንዉን ወቅት ስራዉ የሚጠይቀውን ዕውቀት እና ክህሎት የስልጠና መመሪያዎችን በመከተል ትክክለኛ እና ጥራቱን ብሎም ሚስጥራዊነትን በመጠበቅ እንዲሁም በማስጠበቅ መረጃ በመሰብሰብ አስፈላጊዉን ሁሉ ማከናወን እንዳለባቸዉ ገልፀዋል።
የስልጠናው ዓላማ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዘርፍ የጎላ ፋይዳ ያላቸውን የስታቲስቲክስ መረጃዎች በጥራት በመሰብሰብ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል የሚያስችል የሰው ሀይል ለማዘጋጀት ታስቦ የሚሰጥ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በመጡ የስልጠናው አስተባባሪዎች ስልጠናውን አስመልክቶ ለሰልጣኞች ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ዕውቀት
ለልህቀት
ወራቤ
ዩኒቨርሲቲ
መረጃዎቻችንን
በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!
• Website: https://www.wru.edu.et/
• Telegram: https://t.me/werabeuniversitywru
• YouTube: https://www.youtube.com/@werabeuniversityofficialtu8944